ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛውን ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በይፋ አስጀመሩ

1 Yr Ago
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛውን ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በይፋ አስጀመሩ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል በይፋ አስጀምረዋል።
 
ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለተኛው ምዕራፍ የዘንድሮውን ጨምሮ 25 ቢሊየን ችግኝ በመትከል በቀጣይ አራት አመታት ውስጥ የተተከለውን የችግኝ ብዛት 50 ቢሊየን በማድረስ አካባቢ የመጠበቅ አኩሪ ገድልን መፈጸም እንችላለን ብለዋል።
 
ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በተቀናጀና በተደመረ መንገድ መልካምና አረንጓዴ አካባቢን ለትውልድ በማስተላለፍ ቁም ነገር ሊሠራ ይገባዋልም ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ለነገ ዛሬን ሊተክሉ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አሥተላልፈዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top