ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ የ220 ኪ.ሜ መንገድ ሊገነባ ነው

2 Days Ago
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ የ220 ኪ.ሜ መንገድ ሊገነባ ነው
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኝ የ220 ኪሎ ሜትር መንገድ ሊገነቡ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
 
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ በግንቦት 2023 የተፈራረሙትን የ738 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተከትሎ ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኝ 220 ኪሎ ሜትር መንገድ ሊገነቡ መሆኑ ነው የተገለጸው።
 
የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የሽግግር ሕግ አውጪ ምክር ቤት የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻጋሪ መንገድ ለመገንባት የተፈረመውን የገንዘብ ስምምነት አጽድቋል።
 
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል እያደገ ያለውን ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት በማሳደግ፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
 
ስምምነቱ በጉባዔው በሙሉ ድምጽ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የመጨረሻ ፍቃድ መቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top