የቀድሞ ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮግራም ላይ የሚመክር ውይይት እየተካሄደ ነው

18 Days Ago
የቀድሞ ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮግራም ላይ የሚመክር ውይይት እየተካሄደ ነው
የቀድሞ ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮግራም ላይ የሚመክር ውይይት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
በውይይቱ ላይ የፌደራል መንግስት ተወካይ፣ የትግራይ ክልል ተወካይ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ኃላፊ ተገኝተዋል።
የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ የጋራ የምክክር መድረኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በመቐለ እንዲካሄድ የተደረገበት ዋናው ዓላማ ከተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ በክልሉ የተረጋጋ ሁኔታ በመኖሩ ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ክልል ተወካይ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የምክክር መድረኩ ሰላምን ከማጠናከር ባሻገር ሰፋ ላለ የተሃድሶና የመልሶ ግንባታ ስራ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ኃላፊ ሚስተር ቱርሃን ሳለ በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው የቀድሞ ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋሚያ መርሐግብር ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን ይወጣል ብለዋል።
በሰለሞን ፀጋዬ
ግብረመልስ
Top