ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ አራተኛውን የግብርና ልማት የግምገማ ሪፖርት አቀረቡ

6 Mons Ago 1050
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ አራተኛውን የግብርና ልማት የግምገማ ሪፖርት አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ አጠቃላይ የግብርና ልማት ፕሮግራም መሪነታቸው በፕሮግራሙ በየሁለት አመቱ ከሚቀርበው የግምገማ ሪፖርት አራተኛውን ለኅብረቱ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥት አቅርበዋል።

የአፍሪካ አጠቃላይ የግብርና ልማት ፕሮግራም ለአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ ሀብት ፈጠራ፣ የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት፣ የምጣኔ ሀብት እድገት እና ብልጽግና የፓሊሲ ማዕቀፍ ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ዕድገት የሪፖርታቸው አካል በማድረግም ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለከክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top