የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራኢስ ፓኪስታንን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ

1 Mon Ago 228
የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራኢስ ፓኪስታንን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ

የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራኢስ ከሰኞ እስከ እሮብ ባሉት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት በፓክስታን ሊያደርጉ መሆኑን የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸ፡፡  

ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት የሻከረ ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነታቸውን ለመጠገን የፈለጉት በጥር ወር በፓኪስታን የደረሰውን የሚሳኤል ጥቃት ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ከሳምንት በፊት ኢራን በኢስራዔል ላይ ያልተጠበቀ በሚሳኤል ሮኬት የተደገፈ ጥቃት መሰንዘሩዋን ተከትሎ ኢስራኤል ደግሞ በምላሹ አርብ ዕለት የበቀል እርምጃ ጥቃት በቴሄራን ላ መውሰዷ ተጠቅሷል፡፡

ይህንን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውጥረቱ ተባብሷል ነው የተባለው፡፡

ውጥረተን ለማርገብ እና ይህን ተከትሎ የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ረኢስ ኢስላማባዲን ልጎበኙ እንደሚችሉ በፓክስታን ጠቅላይ ሚኒስትር በኩል ተገልጿል፡፡

ኢብራሂም ራኢስ በጉኝታቸው የፓኪስታኑን ፕሬዝደንት፤ ጠቅላይ ሚንስትሩን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩንና የሀገሪቱን ምክር ቤት ሊቀመንበር እና አፈ ጉባዔውን አግኝተው እንደሚያነጋግሩ የፓክስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሮይተርስ ገልጿል፡፡

ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራኢስ በጉኝታቸው ቀጠናዊ ፣ዓለም አቀፋዊ የልማትና የሁለትዮሽ የንግድ ትብብርና የሽብር አደጋ በተመለከተ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ቴሄራን ለእስራዔል የበቀል እርምጃ ምላሽ ባለመስጣት የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ወደ ቀጠናዉ እንዳይስፋፋ ሚናዋን ተወጥታለች ብሏል ሮይተርስ በዘገባው፡፡

ኢብራሂም ራኢስ የሁለትዮሽና የንግድ ግኑኝነት ለማጠናከር በፓኪስታን ላሆርና ካራቺ የተባሉ ሁለት ከተሞችን በዋናነት ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ሁሉም ወገኞች ግጭቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡና  ገደብ እንዲያበጁ ፓኪስታን ጥር አቅርባለች፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top