በሳውዲ አረቢያ የተከሰተው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ

7 Mons Ago 5192
በሳውዲ አረቢያ የተከሰተው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top