26ኛው የመላ ኦሮሚያ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አገኘ

8 Mons Ago 919
26ኛው የመላ ኦሮሚያ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አገኘ

ተቋርጦ ከቆየ 5 ዓመታትን ያስቆጠረው የመላ ኦሮሚያ ጨዋታዎች ባለፉት ቀናት በጅማ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ዛሬ በነበረው የመዝግያ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቲዎስ ሠቦቃ፤ ከ5ሺ በላይ ስፖርተኞችን በ21 የተለያዩ ውድድሮች ሲያወዳድር የቆየው ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ዛሬ በተደረገው የወንዶች እግር ኳስ የፍፃሜ ጨዋታ ጅማ ዞን ጅማ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በዚህ ውድድር የኦሎምፒክ አጠቃላይ አሸናፊ ሸገር ከተማ ሲሆን አዳማ ከተማ እና ማያ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

የፓራ ኦሎምፒክ አጠቃላይ አሸናፊ አሰላ፤ የዲፍ ኦሎምፒክ አጠቃላይ አሸናፊ ደግሞ የነቀምቴ ከተማ በመሆን ውድድሩ ተጠናቅቋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top