ኢትዮጵያ በመጭው መስከረም የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን እንደምታካሂድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ

10 Days Ago
ኢትዮጵያ በመጭው መስከረም የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን እንደምታካሂድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ

በመጭው መስከረም "ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን - አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታውቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄዱን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት መስራች ሀገር ይህንን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀውን የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ሲሉም ጠቅሰዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top