የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን ከፍጻሜ ለማድረስ ርብርብ ይደረጋል፡- ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

11 Days Ago
የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን ከፍጻሜ ለማድረስ ርብርብ ይደረጋል፡- ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ከፍጻሜ ለማድረስ ርብርብ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
 
የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት የግድቡን የስራ እንቅስቃሴ ዛሬ ተዘዋውረው ተመልከተዋል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅቱ እንደተናገሩት፤ የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ግድብ ግንባታ ከፍተኛ በጀት ተይዞለት የተጀመረ የልማት ፕሮጀክት ነው፡፡
 
ፕሮጀክቱ ከአካባቢው መልክዓ ምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነት ጀምሮ የግንባታ አቅርቦትና የፋይናንስ እጥረት እንዲሁም በተቋራጮች የአቅም ማነስና ተነሳሽነት ችግሮች ሳቢያ መጓተቶች አጋጥሞት መቆየቱን አውስተዋል፡፡
 
አሁን ላይ የግንባታው አፈጻጸም 68 በመቶ የደረሰ ሲሆን በተለይ የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት በመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱ ያጋጠሙትን ማነቆዎች በዝርዝር በመፈተሽ የክልሉና የፌዴራል መንግስት በተናጠልና በጋራ የድርሻቸውን የሚወጡበትን አሰራር እንደሚዘረጋም ተናግረዋል፡፡
 
የጎንደር ከተማ አስተዳደር በኢንቨስትመንትና በመሰረተ ልማት ዘርፍ እያከናወናቸው የሚገኙ የልማት ስራዎችም አበረታች መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡
 
በጉብኝቱ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ የክልልና ከተማ አስተዳደሩ የአመራር አባላት የተሳተፉ ሲሆን፤ በከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top