ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገለፁ

3 Hrs Ago 38
ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገለፁ

ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በፖለቲካ፣ ንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮረው የሁለቱ ሀገራት 3ኛ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ውይይቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ መርተዋል።

ውይይቱ የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዝ ፖለቲካዊ ምክክርን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።  

ሀገራቱ በንግድ፣ በኃይል እና በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ውይይቱ ያግዛልም ነው የተባለው።

ከውይይቱ በኋላ ሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል።

የአዘርባጃን ልዑክ በሚኖረው ቆይታ ከፌደራልና ከክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመምከር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዝ ምልከታ እንደሚያደርግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገልፀዋል።

በዘሃራ መሃመድ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top