የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎትና ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር የፍልሰት መረጃን መጋራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) በስምምነቱ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ የፍልሰት አስተዳደርን በማሳለጥ ከፍልሰት የሚገኘውን ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ ፋይዳዎችን ለመጠቀም ያስችላል፡፡
መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ያግዛል ብለዋል፡፡
የአስተዳደር መዛግብቶች በተለያየ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ባልተደራጀና በተበታተነ መልኩ የሚገኙ በመሆናቸዉ በቀጥታ ለስታቲስቲክስ ልማት መጠቀም አዳጋች ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
በዚህም ከ2011ዓም ጀምሮ የፍልሰት መረጃን ከአስተዳደር መዛግብት ማመንጨት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
የፍልሰት መረጃውን በብሔራዊ ደረጃ ለማደራጀት ስምምነቱን የፈረሙ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በስምምነቱ የሁሉም ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የዘገበው ኢ ፕ ድ ነው፡፡