ኢትዮጵያ የ2025 የብሪክስ ፕሬዚደንትነት ለተረከበችው ብራዚል የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አስተላልፋለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ብራዚል በብሪክስ ፕሬዚደንትነት ጊዜያዋ ፍትሃዊ፣ አካታች እና ውጤታማ የአለምአቀፍ አስተዳደርን ለማስቀጠል የሰነቀችውን ራዕይ እንደምትደግፍ አስታውቋል፡፡
ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለመፍጠር እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ እንደምትሻም ገልጿል።
ኢትዮጵያ በ2025 የብሪክስ ፕሬዚደንትነትን ከተረከበችው ብራዚል ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡
ሩሲያ በ2024 የብሪክስ ፕሬዚደንትነት ጊዜዋ ለሰጠችው አርአያነት ያለው አመራር ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳላትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጨምሮ ገልጿል።