ኢቢሲ ባከናወናቸው ተግባራት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ችሏል - አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

5 Hrs Ago 22
ኢቢሲ ባከናወናቸው ተግባራት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ችሏል - አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

ኢቢሲ ባከናወናቸው ተግባራት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለፁ፡፡

ኢቢሲ በጅግጅጋ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ መፍጠር በሚያስችለው ቅድመ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በዚህ ወቅት፤ ኢቢሲ ከለውጡ ወዲህ በክልሉ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል።

ኢቢሲ በክልሉ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላምና የልማት ስራዎች ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ማስቻሉን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዚህም የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ኮርፖሬሽኑ በክልሉ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ለመፍጠር እያደረገ የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በውይይቱ የኢቢሲ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የቋንቋዎች ዘርፍ ሀላፊ ሙክታር ሁሴን፤ ኢቢሲ ከ150 በላይ ማሰራጫዎች ያሉት ቀደምት ሚዲያ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ "ኢቢሲ ወደ ይዘት" በሚል መርህ የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያዎች በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ በቆዳ ስፋት እና በህዝብ ቁጥር ሰፊ በሆነው የሶማሌ ክልልም ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ለመፍጠር በሚያስችሉ ስራዎች ላይ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በቴዎድሮስ ታደሰ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top