ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው አደጋ የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ

6 Hrs Ago 27
ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው አደጋ የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ

ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በአደጋው የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው መረጋጋገጡን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻውን ከየመን ወደ ጅቡቲ 320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር ዳርቻ አከባቢ ሲደርሱ በደረሰው አደጋ የዜጎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

አደጋውን ተከትሎ 48 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 197 ፍልሰተኞች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸው ተጠቅሷል።

የተቀሩት 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ስራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉ ተጠቁሟል። 

እስከአሁን በስፍራው በተደረገው የዜጎች ማጣራት ሂደት ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ መቻሉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

ኤምባሲው በዚህ ከባድ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ባጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት በየጊዜው እያደረሰ ያለውን ሞት ለመቀነስ ሁሉም ተቋማት በርብርብ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top