በጃፓን ወደ ህዋ እየመጠቀ የነበረ ሮኬት በአየር ላይ ሳለ መፈንዳቱ ተገለፀ

1 Mon Ago
በጃፓን ወደ ህዋ እየመጠቀ የነበረ ሮኬት በአየር ላይ ሳለ መፈንዳቱ ተገለፀ

በጃፓን በሚገኝ የግል ኩባንያ የተሰራ ሮኬት ወደ ህዋ እየመጠቀ በነበረ ወቅት ከሰኮንዶች የአየር ላይ ቆይታ በኋላ መፈንዳቱ ተገልጿል፡፡

ስፔስ ዋንስ ካይሮስ በተባለ የግል ኩባንያ የተሰራው ይህ ሮኬት ለጃፓን መንግስት ለስለላ አገልግሎት የሚውል ሳተላይትን በምህዋር ላይ እንዲያስቀመጥ ታስቦ የተወነጨፈ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

በጃፓን ለመጀመሪያ ጊዜ በግል ኩባንያ የተሰራው ሮኬቱ 18 ሜትር ርዝምት ያለው እና 23 ቶን እንደሚመዝንም ተጠቁሟል፡፡

ሮኬቱ በምዕራብ ጃፓን በሚገኘው ዋካያማ ግዛት የምርምር ማዕከል ከተወነጨፈ በኋላ ለጥቂት ሰኮንዶች አየር ቆይቶ ባልታወቀ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ሊፈነዳ መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

ቶክዮ መቀመጫውን ያደረገው የስፔስ ዋንስ ካይሮስ ኩባንያ አደጋውን አስመልክቶ የገለጸው ነገር ባይኖርም፤ በሮኬቱ ፍንዳታ በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ እና ተነስቶ የነበረው እሳትም በቁጥጥር ስር መዋሉን የኩሺሞቶ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ባለፈው የፈረንጆቹ ሃምሌ ወር ሌላ የጃፓን ሮኬት ወደ ወደ ህዋ እየመጠቀ በነበረ ወቅት ከ50 ሰኮንዶች የአየር ላይ ጉዞ በኋላ ተመሳሳይ ፍንዳታ ደርሶበት እንደነበር ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top