በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ ነው - አቶ እንዳሻው ጣሰው

1 Yr Ago 1323
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ ነው - አቶ እንዳሻው ጣሰው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፈጣን ዕድገት ለማረጋገጥና የህዝብን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

የሀይሴ፣ ሂርቆ ጀማያ 39 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድና ድልድይን ጨምሮ በሀድያ ዞን በክልሉ መንግሥትና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነቡ ፕሮጀክቶች ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው በፕሮጀክቱ ምርቃ ላይ እንደገለጹት፥ የክልሉ መንግሥት ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ስራዎችን በማከናወን በክልሉ ፈጣን ዕድገት ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው።

የክልሉ ማህበረሰብ በተለይ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ አምራች እንደሆነና ከክልሉ አልፎ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ያመረተውን ምርት በቀላሉ ለገበያ ማቅረብ እንዲችል የመንገድ መሰረተ ልማትን ተደራሽ የማድረግ ሥራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑም ገልጸዋል።

አቶ እንዳሻው እንዳሉት፥ መንግሥትና ህብረተሰቡ ተቀናጅተው መስራት ከቻሉ አመርቂ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በዛሬው ዕለት የተመረቁ ፕሮጀክቶች ማሳያዎች ናቸው።

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት ፈጣን እድገት ለማረጋገጥና ለህዝብ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዛሬ ለምረቃ የበቃው የሀይሴ፣ ሂርቆ፣ ጀማያ መንገድና የለሜጃ ድልድይ ከፍተኛ አምራች የሆነውን የአካባቢውን ማህበረሰብ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ሲገጥመው የነበረውን የመንገድ ችግር ያቃልላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top