በኢቢሲ ቤተሰብ እግር ኳስ ውድድር ኢቢሲ የገቢዎች ሚኒስቴርን በማሸነፍ ለዋንጫ አለፈ

11 Mons Ago
በኢቢሲ ቤተሰብ እግር ኳስ ውድድር ኢቢሲ የገቢዎች ሚኒስቴርን በማሸነፍ ለዋንጫ አለፈ

በኢቢሲ ቤተሰብ እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ የገቢዎች ሚኒስቴርን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለዋንጫ አልፏል።

አዲሱን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሚዲያ ኮምፕሌክስ ምርቃትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የኢቢሲ ቤተሰብ እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ነው።

ረቡዕ ዕለት በተደረገው ጨዋታ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ወጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፉ ይታወሳል።

በመሆኑም የውድድሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋንጫውን ለማንሳት የሚፋለሙ ይሆናል።

ይህ ውድድር፣ ኢቢሲ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር ከመሥራት ባለፈ ስፖርታዊ ፉክክርም ለማድረግ ያለመ ቤተሰባዊ የስፖርት ውድድር ነው።

በላሉ ኢታላ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top