ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ

6 Mons Ago
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ዛሬ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሚኒስትር ዴኤታው ታረቀኝ ቡሉልታ ተገኝተዋል።

ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015” ዛሬ ይጠናቀቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገር አቀፍ ኤክስፖውን መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።

በኤክስፖው ላይ 124 አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዳቀረቡም ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top