ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ 15ኛው የአፋር ህዝብ ሱልጣን ሆኑ

15 Days Ago
ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ  15ኛው የአፋር ህዝብ ሱልጣን ሆኑ
የአፋሩ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሲመት ስነ ስርዓት በአሳይታ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
የሱልጣኑ በዓለ ሲመት መካሄዱን ተከትሎ 15ኛው የአፋር ህዝብ ሱልጣን ለመሆን ችለዋል።
ሱልጣን አህመድ አሊ ሚራህ የሱልጣንነት ሲመት ላይ ለመገኘት ከሚኖሩበት አሜሪካ ሀገር አፋር በቅርቡ የገቡ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የአፋር ህዝብ ሱልጣን የነበሩትና ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ሀንፍሬህ አሊሚራህ ወንድም ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከጅቡቲና ከኤርትራም በርካታ እንግዶች ታድመዋል።
በተስፋዬ ጫኔ

ተያያዥ ርዕሶች

ግብረመልስ
Top