ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ የናይጀሪያ ተመራጭ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

1 Yr Ago
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ የናይጀሪያ ተመራጭ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ለተመረጡት የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ “የቲኑቡ ለፕሬዚደንተነት መመረጥ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን የጠበቀ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል“ ሲሉ መግለጻቸውን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትውተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል።

የ70 ዓመቱ ቦላ አህመድ ቲኑቡ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መሆኑ ይታወቃል።

 
 
 
 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top