የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

1 Mon Ago 273
የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፈተናው ከሚሰጥባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዲ በሆነው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የፈተና አሰጣጡን ተመልክተዋል፡፡

ፈተናው በኮምፒውተር (online) እና በወረቀት እየተሰጠ ይገኛል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በመላው ሀገሪቱ በጥሩ ሁኔታ እየከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፈተና አሰጣጡ የተሳካ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህም የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማድረግ እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ በበኩላቸው ፈተናው ከመሰጠቱ በፊት ለተማሪዎች አስፈላጊው ገለፃ መደረጉን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም ተፈታኞች በፈተና ወቅት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ እና መብት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው በፈተና ቆይታቸው ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ህገ-ደንቦችን በሚመለከት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም በዩኒቨርሲቲው 4ሺህ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top