ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እናመሰግናለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

4 Mons Ago 667
ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እናመሰግናለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፤ በጤና እና የፋይናንስ ዘርፉን አካታች ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ቢል ጌትስ ከ2010 ዓመተ ምህረት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ እንኳን ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ መጡ ብለዋል።

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፤ በጤና እና የፋይናንስ ዘርፉን አካታች ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ለሚያደርግልን ያልተቋረጠ ድጋፍ በጣም እናመሰግናለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የዛሬው በስንዴ ክላስተር ልማት እና የዶሮ እርባታ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን በመቻል ጥረት መንገዷን አጽንታ ባለበት ወቅት የተጠናከረውን ትብብር የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top