በህንድ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 158 ማለፉ ተገለፀ

1 Mon Ago 454
በህንድ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 158 ማለፉ ተገለፀ
በደቡባዊ ህንድ ኬራላ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ158 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡
በተከሰተው አደጋ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ እስካሁን ሊገኙ እንዳልቻሉም ነው የተገለጸው፡፡
የሃገሪቱ መከላከያ ሰራዊት፣ ባህር ሃይል፣ ፖሊስ እና እሳት አደጋ በጋራ በመሆን የነብስ አድን ስራውን እየሰሩ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም 45 የሚሆኑ የእርዳታ ካምፖች የተቋቋሙ ሲሆን ከአደጋው የተረፉ ከ5 ሺህ 000 በላይ ሰዎች ወደ ካምፑ እንደገቡ ተገልጿል፡፡
በአካባቢው በከባድ ሁኔታ እየጣለ ያለው ዝናብ የነብስ አድን ስራው ቀላል እንዳይሆን ማድረጉ ቢገለጽም፤ ከአደጋው እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በህይወት መታደግ መቻሉ ተጠቅሷል፡፡
አደጋውን ተከትሎ በኬራላ ግዛት የሀዘን ቀን መታወጁንም ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል፡፡
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top