የምድራችን ትልቁ የደን መገኘ የሆነው አማዞን እንደሃገር ቢጠራ የአለማችን 8ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር፡፡
- አብዛኛው የደኑ ክፍል በብራዚል የሚገኘው የአማዞን ጫካ ለምድራችን የዓየር ንብረት ሚዛን መጠበቅ ጉልህ ሚና አለው፤ በዚህም የምድራችን ሳንባ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
- አማዞን 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ይህም የህንድን ቆዳ ስፋት ሁለት እጥፍ እንደማለት ነው፡፡
- 9 ሀገራትን ከሚያካልለው የአማዞን ጫካ 60 በመቶ የሚሆነውን ብራዚል ስትይዝ የተቀረውን ፔሩ፣ ኮሎምቢያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር፣ ቦሊቪያ፣ ጉያና፣ ሱሪናሜ እና የፈረንሳይ ጉያና በተለያየ መጠን ይጋሩታል፡፡
- ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነውን የምድራችንን ኦክስጅን የሚዘጋጅበት አማዞን፤ ከፍተኛ የሆነ የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን በመሰብሰብ ለዓየር ንብረት መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
- ከ400 ቢሊዮን በላይ ዛፎች በውስጡ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም 16ሺህ በሚደርሱ የዝርያ አይቶች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡
- ደኑ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ እጽዋቱ ጸሃይየሚያገኙትከ2 እስከ 5 በመቶ ብቻ ሲሆን ይህም ጫካው ጨለም ያለ የብርሃን መጠን እንዲኖረው አድርጓል፡፡
- ጫካው ከሚያገኘው የዝናብ መጠን ግማሽ ያህሉን ትራንስፓይሬሽን በተባለ ሂደት በራሱ ያመነጫል፡፡
- በእርጥበታማው ወቅት ነጎድጓዳማ ዝናብን የሚስተናግድደው የአማዞን ጫካበየዓመቱ 50 ሚሊዮን የሚሆን መብረቅን እንደሚያስተናግድም ይነገራል፡፡
- ይህም በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘውን ናይትሮጅን በመሰባበ ርበዝናብ መልክ እንዲወርድ በማደረግ ለማዳበሪያነት እንዲጠቀመው ያግዘዋል፡፡
- በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በደኑ ውስጥ ያሉ ዛፎች “የእንጨትሰፊድር” (Wood Wide Web) በመባል በሚታወቀው የምድር ውስጥ የፈንገስ አውታር አማካኝነት እርስ በርስ መገናኘት ይችላሉ።
- ይህአውታረ በጫካው ያሉ ዛፎች በስሮቻቸው አማካኝነት ንጥረ ምግቦችን እንዲካፈሉ እና ከአደጋዎች ለማስጠንቀቅ ያስችለዋል።
- በጫካው ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ ነብሳት፣ ከ2ሺህ በላይ በራሪ እና አጥቢ እንስሳት እንዲሁም በ10ሺህ የሚቆጠሩ የእፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡
- ጫካው በውስጡ ከያዛቸው በርካታ እና ልዩ ብዝሃ ህይወት በተጨማሪ ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፅዋት መገኛ ነው፡፡
- 7 ሺህ 62 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የምድራችን 2ኛው ረጅሙ ወንዝ የሆነው የአማዞን ወንዝ የሚገኘው በዚሁ ጫካ ውስጥ ነው፡፡
- 400 የሚደርሱ ጎሳዎች በጫካው ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ፣ ስለደኑ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳላቸው ይጠቀሳል ፡፡
- ከጫካው በደቂቃዎች ውስጥ ከ 5 የእግር ኳስ ሜዳዎች ጋር የሚመጣጠን ያህል ደንይቆረጣል።
- በዚህም አሁን ላይ 17በመቶ የሚሆነው የደኑ አካል መውደሙ ይገለፃል፡፡
- ይህም ደኑን ወደ ቀድሞ ይዞታው መመልስ እስከማይቻልበት ጫፍ ላይ ሊያደርሰው እንደሚችል የተመራማሪዎች ስጋት ነው፡፡
በአፎሚያ ክበበው