በ3ኛ ዙር ወደ ሀገራቸው ለሚገቡ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሚደረገው አቀባበል ተጀምሯል

1 Mon Ago 221
በ3ኛ ዙር ወደ ሀገራቸው ለሚገቡ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሚደረገው አቀባበል ተጀምሯል
በሦስተኛ ዙር ወደ ሀገራቸው ለሚገቡ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሚደረገው አቀባበል መጀመሩን የቱሪዚም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
“Leave your Legacy, savor your holiday” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ በሦስተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን፣ የእረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አማካኝነት አሻራቸውን የሚያኖሩበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
 
2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንኑ፤ የተቸገሩ ወገኖቻቸውን የሚያገዙበት፣ የቀሰሙትን ትምህርትና ልምድ ለወገኖቻቸው የሚያሸጋግሩበት እና የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን በመጎብኘትና በመዝናናት መልካም ትውስታን ይዘው የሚመለሱበት የማጠቃለያ ምዕራፍ መሆኑ ም ተጠቅሷል፡፡
 
ይህ ምዕራፍ እስከ መስከረም አጋማሽ እንደሚቆይ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያየ ዓለም ለሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን እንዲጎበኙ ባደረጉት ጥሪ መሰረት በሁለት ዙሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መምጣታቸው ይታወቃል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top