• “በወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ ቢታይልን”- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች *********** • “የምርቶቹን ዋጋ ማረጋጋት ቀጣይ የቤት ስራዬ ነው“- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

14 Days Ago
• “በወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ ቢታይልን”- የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ***********                        • “የምርቶቹን ዋጋ ማረጋጋት ቀጣይ የቤት ስራዬ ነው“- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
የበዓል ወቅት መድረሱን ተከትሎ ኢቢሲ በተመረጡ የመዲናዋ ገበያዎች የመሰረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ቅኝት አድርጓል፡፡
 
በቅኝቱ ወቅት ያነጋገራቸው ሸማቾች በአትክልት እና ፍራፍሬ ላይ የታየው የዋጋ መረጋጋት ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል፡፡
 
በአንጻሩ የወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ መፍትሔ እንዲበጅለትም አሳስበዋል፡፡
 
ኢቢሲ ሳይበር በቅኝቱ፤ ቅቤ በአማካኝ 950 ብር፣ ቆጮ በኪሎ 130 ብር፣ የፈረንጅ እንቁላል 8 ብር፣ የሐበሻ እንቁላል 14 ብር፣ አይብ ከ550 ብር ጀምሮ፣ የሐበሻ ዶሮ ከ1 ሺህ ብር ጀምሮ፣ የፈረንጅ ዶሮ ከ500 ብር ጀምሮ እንዲሁም በግ ከ8 ሺህ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ መሆናቸውን ተመልክቷል፡፡
 
“የወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶችን ዋጋ ለማረጋጋት ምን እየሰራችሁ ነው?” ሲል አቢሲ ሳይበር የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ፤ ቢሮው ውጤት የተገኘባቸውን የአትክልት እና ፍራፍሬ የዋጋ ማረጋጋት ስራዎች በወተት እና የወተት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ ለመድገም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ለዚህም ምርቶቹ ወደ ገበያ ከገቡ በኃላ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉበት የማቀዝቀዣ ስርዓት እየታሰበበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
 
ኃላፊው አትክልት እና ፍራፍሬ ላይ በቂ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት መገኘቱን አበክረዋል፡፡
 
ከዚህ ቀደም የገበያ ሰንሰለቱ መርዘም ለዋጋ ንረት አይነተኛ ምክንያት እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፤ አሁን ላይ አምራች እና ሸማቹን በቀጥታ የማገኛኘት ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጣቸው አንስተዋል፡፡
 
በዚህም ሽንኩርት በአማካኝ ከ50 እስከ 55ብር፣ ቲማቲም 20 ብር፣ ሎሚ በኪሎ 120 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት ከ250 ብር እስከ 280 ብር ለገበያ በመቅረብ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በመዲናዋ የገበያ ማዕከላት ቁጥር መጨመር፣ ምርት የማምረት እንቅስቃሴዎች መጠናከር እንዲሁም የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን ለገዢዎች በአግባቡ ማቅረብ መቻል ቢሮው ከመደበኛው የገበያ ዋጋ ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ አድርጎ የዋጋ ተመን እንዲቆርጥ ማገዙን አስታውቀዋል፡፡
 
ለሰብል ምርቶችም ምቹ ቦታን በማዘጋጀት በቀጣይ በሁሉም የገበያ ማዕከላት እንዲገኙ እየሰተሰራ መሆኑንም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ተናግረዋል፡፡
 
አፎሚያ ክበበው
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top