የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና የሰራዊት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ኢትዮጵያ ለአንድነቷ እና ለሉዓላዊነቷ ታላቅ መስዋዕትነት እና ገድል የተሰራላት ትልቅ የጀግንነት ታሪክም ያላት ሀገር መሆኗ የታየበት ነው ብለዋል፡፡
መታሰቢያው የአልበገር ባይነትን፤ የአንድነት፤ የነጻነት ፋና ወጊ እኛ ኢትዮጵያውያኖች እንደመሆናችን መጠን ይህን ተግባር ለትውልድ ለማሻገር መከላከያ ሰራዊታችን ለትውልድ የሚሰራው ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደ መከላከያ ሰራዊት በአባቶቻችን ጀግንነት እንድንኮራ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ልዩ የሞራል እና የአገር አደራ ስንቅ የሚሰጥ ነውም ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።