ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ገለፀች

3 ወር በፊት
ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ገለፀች

በሩሲያ መዲና ሞስኮ በተጀመረው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች የዓመቱ የመጀመሪያ ከፍተኛ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች። 

በጉባኤው ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያን ወክለው በመሳተፍ ላይ ናቸው። 

አቶ ማሞ ምህረቱ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የኢኮኖሚ ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። 

ብሪክስ ኢትዮጵያ ለተያያዘቻቸው የልማት ስራዎች አዳዲስ እድሎችን ይፈጥራል ያሉት አቶ ማሞ፤ ምጣኔ ሀብትን በማዘመን፣ የፋይናንስ ጉድለትን በመሙላት እና የኢንቬስትመንት መዋዕለ ንዋይን በማሳደግ ተጨማሪ የልማት ግብዓቶችን እንደሚፈጥር ገልፀዋል። 

የባለብዙወገን ተቋማት አካታች፣ ፍትሃዊ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል። 

ጉባኤው የባለብዙ ወገን ግንኙነትን በማጠናከር ፍትሃዊ ዕድገት እና ደህንነትን በዓለም ዙሪያ ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እየመከረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top