"የትርክት ዕዳና በረከት" የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመረቀ

5 Mons Ago 1671
"የትርክት ዕዳና በረከት" የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመረቀ

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተፃፈው "የትርክት ዕዳና በረከት" መፅሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመፅሃፍ ምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያዊያን ያለንበት መከራ እና የገጠመን አሳሳቢ በሽታ ትርክት የወለደው ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ታሪክ የምንማርበት እንጂ እስረኛ ሊያደርገን አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሌሉ ገዢዎች ልንጣላ አይገባንም ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት "የትርክት ዕዳና በረከት" የመጽሐፍ ምረቃ ላይ በጎፋ ዞን በደረሰው አስከፊ አደጋው ህይወታቸው ላጡ ዜጎች የህሊና ፀሎት አድርገዋል።

በሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈው "የትርክት ዕዳና በረከት" መጽሐፍ ምረቃ ላይ ከታደሙ ግለሰቦች ለተነሱ ጥያቄዎች ደራሲው ምላሽ መስጠታቸው ተጠቅሷል።

የመፅሐፉ የምረቃ መርሐ - ግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ መከናወኑንም ተጠቁሟል።

"የትርክት ዕዳና በረከት" መፅሐፍ በ46 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ 575 ገፆች ያሉት ነው፡፡

በአሸናፊ እንዳለ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top