አምስት ሚሊዮኖቹ ኮደሮች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ፤ ለአህጉራችን የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቁ ጭምር ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

1 Mon Ago 588
አምስት ሚሊዮኖቹ ኮደሮች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ፤ ለአህጉራችን የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቁ ጭምር ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ"ን ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምረዋል። 

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ወደፊት የሚያልሙ አሳቢ ወጣት ዜጎቿ ተስፋ አላት ብለዋል። 

ዛሬ በይፋ የጀመርነው የ"አምስት ሚሊዮን ኮደሮች" መርሃግብር ታላቅ እድል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወጣቶች በመርሃግብሩ በመመዝገብ ክህሎት እና ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ሁሉም እንዲያበረታታ ጥሪ አቅርበዋል።

አምስት ሚሊዮኖቹ ኮደሮች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ፤ ለአህጉራችን የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቁ ጭምር ናቸው ብለዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ ለታላቁ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ትብብር ያደረገውን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥትን አመስግነዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top