በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

8 Mons Ago 588
በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።
 
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ሐሰተኛ ሰነድ ያላቸው እና ምንም ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች መኖራቸውን በተደረገ ማጣራት አረጋግጠናል ብለዋል።
 
እነዚህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያነሡት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሰነዳቸውን ሕጋዊ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ይህንኑ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በተለያየ ምክንያት ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ዜጎች ለማጣራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
 
በኢትዮጵያ ዜጎች እየተጠቀሙበት የሚገኘውን ፓስፖርት ኤሌክትሮኒክ (ኢ-ፓስፖርት) ለማድረግ እና ለማዘመን እየተሠራ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።
 
በመሐሪ ዓለሙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top