የኢትዮጵያ ሰላም የሚረጋገጠው በህዝቦች የነቃ ተሳትፎና በፀጥታ ኃይሉ ቅንጅት ነው - ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

7 Mons Ago
የኢትዮጵያ ሰላም የሚረጋገጠው በህዝቦች የነቃ ተሳትፎና በፀጥታ ኃይሉ ቅንጅት ነው - ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

የኢትዮጵያና የህዝቦቿ የሉ›ላዊነት፣ የአንድነት እና የሰላም ዋስትና የሚረጋገጠው በህዝቦቿ የነቃ ተሳትፎ እና በፀጥታ ኃይሉ ቅንጅት መሆኑን የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገልጸዋል።

ሌተናል ጄኔራል ሹማ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ከሚሴ ከተማ ከዞን፣ ከወረዳ እና ከአራት የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከሚኒ ካቢኔዎች፣ ከሌሎች የፀጥታ ኃይል አመራሮችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በአካባቢው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሌተናል ጄኔራል ሹማ በመድረኩ፥ የዞኑ ህዝብ ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት አስፈላጊውን መስዋዕትነት እየከፈለ መቆየቱን አስታውሰው፤ ዛሬም በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረውን አሸባሪው ሸኔን ለመመንጠር እያደረገው ላለው አስተዋጽኦ ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል።

ሠራዊቱ አሸባሪው ሸኔን በየቦታው በመደምስስ እያንኮታኮተው እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው፥ አሸባሪው ሸኔን ከመዋጋት አንፃር ውጤታማ ስራ ከመሰራቱ በተጨማሪ በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት 108 የሸኔ አባላት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸውን ገልጸዋል።

ሠራዊቱ እና ሌሎች የዞኑ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ስምሪት 162 የሸኔ ሴሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና በርካቶች መደምሰሳቸውን ገልጸው፤ ሌት ተቀን ለህዝቦች ሰላም እየታተረ እና መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top