ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

7 Mons Ago
ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ ነው

ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ። 

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የጉባዔውን መካሄድ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። 

ጉባዔው "ማህበራዊ ምክክርን እና የጎለበተ ምርታማነትን በመጠቀም ማህበራዊ ፍትህን ማላቅ" በሚል መሪ ሀሳብ ከኅዳር 24 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ብለዋል። 

ጉባዔው ከባለድርሻ አካላት ጋር በአንድነት በመሆን ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ ልምዶች የሚቀመሩበት እና ለዘርፉ መጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ይሆናል ነው ያሉት።      

የዓለም ሥራ ድርጅት ሲቋቋም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት አባል መሆኗን አስታውሰው፤ ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ላይ ሁሌም ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።   

በመስኩ ሥራቸውን በአግባቡ በመከወን ውጤታማ መሆን የቻሉ አካላትና ሠራተኞች ዕውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል።     

ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር ባለው ትብብር የተገኙ ስኬቶች በሚጠናከሩበት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሚፈቱበት አቅጣጫ ላይ የጋራ ሀሳብ የሚያዝበት መሆኑንም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top