የአማራ ክልልን ወቅታዊ ጉዳዮች የሚዳስስ ውይይት በአራት ማእከላት እየተካሄደ ነው

8 Mons Ago
የአማራ ክልልን ወቅታዊ ጉዳዮች የሚዳስስ ውይይት በአራት ማእከላት እየተካሄደ ነው

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች ውይይት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት ባሕርዳርን ጨምሮ በአራት ማዕከላት እየተካሄደ ነው። 

በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ገበያ ተስፋ በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት በርካታ አካባቢዎች በችግር ውስጥ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

የዜጎች እንቅስቃሴ መገደብ እና የልማት እንቅስቃሴዎች መስተጓጎል እንደገጠማቸውም አመላክተዋል።

በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ፅናት እና ቁርጠኝነት የተላበሰ መሪ እና የፀጥታ ኀይል መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በሁሉም አካባቢዎች የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የመልካም አሥተዳደር እና የልማት ሥራዎችን በሚገባ መምራት፣ የኮሙኒኬሽን ግንኙነቱን የተስተካከለ ማድረግ እና የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በብቃት መፈፀም ይገባልም ብለዋል።

እየመጡ ያሉ ለውጦችን በሁሉም አካባቢዎች ወጥ እና ፅኑ ማድረግ እንደሚገባም ተመላክቷል።

አጀንዳ ተቀባይ ከመሆን በመውጣት በተረጋጋ መንፈስ ሥራን መከወን ይገባልም ብለዋል።

በክልሉ ያለውን መሪ በአግባቡ ማደራጀት እና መምራት ይገባልም ተብሏል።

የመሪ እና የሕዝብ አንድነትን መፍጠር ወሳኙ ጉዳይ መሆኑንም ኀላፊዋ ገልጸዋል።

በሥራ እድል ፈጠራ፣ በኑሮ ውድነት እና በምርት ጭማሪ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ወቅቱን የሚመጥን የፖለቲካ ትንተና እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

ለሕዝብ ሰላም እና አንድነት አደጋ የሚሆኑትን መታገል እና ማስተካከል እንደሚገባም አመላክተዋል። ከተለያዩ አደረጃጀቶች እና ማኅበሮች ጋር ስለ ሰላም እና አንድነት መምከር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

ከላይ እስከታች ባሉ መሪዎች የማይፈፅሙትን ለሕዝብ ቃል አለመግባት እንደሚገባም አመላክተዋል።   የክልሉን ሰላም በሚገባ ማረጋገጥ እና ወደተሟላ ሰላም መሄድ ቀጣይ ሥራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለዘላቂ ሰላም ከሕዝብ ጋር አንድነት መፍጠር እንደሚገባም ተናግረዋል።

ከመላው ሕዝብ ጋር ውይይት ማድረግ ቀጣይ ሥራ መሆን ይገባዋልም ብለዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል።

የክልሉን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሕዝብን ሥነ ልቡና ከፍ ማድረግ እና ከስጋት ማላቀቅ እንደሚገባም ኀላፊዋ አመላክተዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top