ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን መመዝገቡን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቀ

11 Mons Ago
ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን መመዝገቡን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቀ

ፕሮግራሙ በተያዘው ዓመት መገባደጃ ላይ ደግሞ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመዘገብ ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን ዩኒት ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል። 

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝግባ በተለያዩ የምዝገባ ጣቢያዎች፣ በአንድነት ፓርክ እንዲሁም በባንኮች በተመረጡ ቅርንጫፎች እየተከናወነ ነው። 

በid.et ዌብ ሳይት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በየዕለቱ የግንዝቤ ማስጨበጫ ስራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ አቤኔዘር ተናግረዋል። 

የብሔራዊ  ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ስትራቴጂ ዋና ዓላማ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቅመው የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማስቻል እንደሆነም ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት። 

ከባንኮች ጋር የዲጂታል መታወቂያን ማቀናጀት ተጀምሯል፤ እስካሁንም በባንኮች በተመረጡ በተመረጡ 8 ቅርንጫፎች የማቀናጀት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል። 

ወደ ፊት ዲጂታል መታወቂያን ከፋይናንስ ሴክተር ጋር በማቀናጀት አንድ ሰው መታወቂያውን ተጠቅሞ የፋይናንስ  አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችል እየሰራን ነው ብለዋል። 

ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር በመተባበር በ14ቱ የገቢዎች ቢሮ የታክስ ቅርንጫፎች የታክስ መለያ ቁጥርን ከዲጂታል ፋይል ቁጥር ጋር ማገናኘት ተጀምሯል። 

በቅርቡም በክልል በሚገኙ የገቢዎች ቢሮዎች የታክስ መለያ ቁጥርን ከዲጂታል ፋይል ቁጥር ጋር የማቀናጀት ስራ እንደተጀመረ አቶ አቤኔዘር ጠቁመዋል። 

በመስፍን ገብረማርያም


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top