ባንኩ በትግራይ ክልል ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው፡ - አቶ ጌታቸው ረዳ

1 Day Ago 137
ባንኩ በትግራይ ክልል ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው፡ - አቶ ጌታቸው ረዳ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ግንባር ቀደም አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን ቀን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ከባለሐብቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
 
በምክክር መድረኩ የተገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ በክልሉ በነበረው ችግር ተቀዛቅዞ የቆየው የኢኮኖሚ እንቀስቃሴ እንዲነቃቃ ባንኩ ያደረገውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
 
የንግዱ ማህበረሰብ ያለውን የፋይናንስ ፍላጎት እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አጥንቶ የሚሰጠውን በጎ ምላሽና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ይብልጥ እንደሚያጠናክር እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
 
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ምህረት በየነ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የክልሉ ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የንግድ ባንክ ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቀሌ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ልሳነወረቅ በበኩላቸው ባንኩ የብድር አገልግሎትን ለማሻሻልና አገልግሎቱን ለማዘመን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም አገልግሎቱን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ዛሬ ባዘጋጀው የደንበኞች አገልግሎት መድረክ በተለያዩ የልማትና የንግድ ስራዎች የተሰማሩ ባለሐብቶች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top