ርዕደ መሬት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

1 Day Ago 118
ርዕደ መሬት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ ነው፡-  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ርዕደ መሬት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመሠረተ-ልማት፣ የጊዜያዊ መጠለያ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የሳይንሳዊ ትንተና እና ትንበያ ቡድኖችን በማደራጀት በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ሁኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተናና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው ብለዋል።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ዛሬ ባደረጉት ጉብኝት በርዕደ መሬት ነክ ሳይንሳዊ ምርምር አበረታች ስራዎች መመልከታቸውን ተናግረዋል።
 
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በርዕደ መሬት ክስተት ዙሪያ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተጠናከረ ተግባር መገባቱንም ጠቅሰዋል።
 
መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት የጥናትና ምርምር ተቋማት ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ኃይል ጠንካራ ቁመና እንዲፈጥሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top