በሠላም ግንባታ ተግባራት ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡- የሠላም ሚኒስቴር

4 Mons Ago 419
በሠላም ግንባታ ተግባራት ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡- የሠላም ሚኒስቴር
የሠላም ሚኒስቴር በሠላም ግንባታ ተግባራት ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።
የሠላም ሚኒስቴር ከፌዴራል፣ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደር የሠላምና የፀጥታ መዋቅሮች ጋር የሚያካሄደው 7ኛው ሀገር አቀፍ የሠላምና ፀጥታ የጋራ ምክክር መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
የሠላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፤በ2016 ዓ.ም ዘላቂ ሠላምን ለመገንባት ብዝሃነትን መሠረት ያደረገ ገዥ ትርክት ለመፍጠር የተሠራው ሥራም ስኬታማ እንደነበር በመድረኩ አንስተዋል።
ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እና ከተከሰቱ በኋላም በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሎች እና በፌዴራል እንዲሁም በክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ፣የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እና የባህል ልውውጥ ሥራዎች ላይ ትኩረት መደረጉ ለሠላም ግንባታ ሥራው አበርክቶ እንደነበረው ጠቅሰዋል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግሥት ለሠላም ግንባታ እና ለሕግ የበላይነት ቅድሚያ ሠጥቶ በመስራቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች አስተማማኝ ሠላም መስፈኑን ተናግረዋል።
በክልሉ አስተማማኝ ሠላም ተረጋግጦ ዜጎች የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው የገለጹት።
የሠላምና የፀጥታ ምክክር ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በነገ ውሎው በስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች በጎረፍ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በመጎብኘትና ድጋፍ በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
በደስታ ወልደሰንበት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top