እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉን በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ ተከላውን የሚስተባብሩት የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ችግኞች እየተተከሉ ከሚገኙባቸው ስፍራዎች የሚመጡ መረጀዎችን በትክክለኛው ቦታ ስለማረፋቸው የማጣራት ስራን ከባለሙዎች ጋር እየተሰራ መሆኑን አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ከ112 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ በ54 ሚሊዮን ሄክታር ላይ የሥርዓተ ምህዳር መጎሳቆል መታየቱን በጥናት አረጋገጥናል ያሉት ሰብሳቢው የመሬት መጎሳቆልንና የደን መጨፍጨፍን ለማስቀረት የችግኝ ተከላ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
ችግኝ ለመትከል እንዲያስችል 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የቦታ ልየታ ስራ ተሰርቶ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ደግሞ ጂኦሪፈረንስ ወይም የካርታ ስራ እንዲኖረው ተደርጓልም ብለዋል፡፡
ዘንድሮ በ317 ሺህ 521 ሄክታር መሬት ላይ የችግኝ ተከላ የሚካሄድ ሲሆን 8454 ቦታዎች በጂኦሪፈረንስ (ካርታ) መለየቱንም ዶ/ር አደፍረስ ተናግረዋል፡፡
የካርታ ሥራ ችግኞች የት እንደተተከሉ ማወቅ ከማስቻሉም በላይ ለምን ዓለማ እንዴት መጠቀም እንዳለብን ለማስተዳደር እንደሚጠቅም ገልጸዋል።
ዘንድሮ 7.5 ቢሊዮን ችግኞች ማፍላት የተቻለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 1.6 ቢሊዮን ችግኞች ሀገር በቀል መሆናቸውን አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል።