የሰውነታችን አስገራሚ እውነታዎች

2 Mons Ago 255
የሰውነታችን አስገራሚ እውነታዎች
  • የእያንዳንዱ ሰው ምላስ አሻራ እንደ እጅ አሻራ የተለየያ እና የማይደገም ነው፡፡
  • ምላስ ከሰውነት የማይደክም አካል ነው፡፡
  • ከሌላው የሰውነት ክፍል በተለየ ጆሮ እና አፍንጫ ማደጋቸውን አያቆሙም፤ በዚህም ነው የሰው ልጅ እድሜ ሲጨምር መጠናቸው ከፍ እያለ የሚሄደው፡፡
  • የተለየ የመሳሳብ ችሎታ ከሌለ በስተቀር ክርንን በአፍ መንካት አይቻልም፡፡
  • በረሃብ ወቅት ከሆድ ውስጥ የሚሰማው ድምፅ "ቦርቦርጊሚ" የሚባል ሲሆን በምግብ መፍጫ ውስጥ በሚኖር የጋዝ እና የፈሳሽ እንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ ነው፡፡ይህም በምግብ መፍጨት ሂደት የተለመደ ነው፡፡
  • ልክ እንደ ጣት አሻራ የሁሉም ሰው ሳቅ የማይደገም፣የተለየ ድምፅ እና ዜማ አለው፡፡
  • በሰውነት ውስጥ የሚገኙ አጥንቶች ያለማቋረጥ የሚሰበሩ እንደገናም የሚገነቡ ሲሆን፤በየ10 ዓመቱ ሙሉ በሙሉ የሚሆነው አጥንት በሌላ ይተካል፡፡ይህም ለአጥንት መጠገን እና መጠናከር ይረዳል፡፡
  • የሰው ልጅ ልብ በቀን 100 ሺህ ጊዜ የሚመታ ሲሆን፤ ከ5-6 ሊትር የሚሆን ደም ይረጫል፡፡
  • የልብ ምት ከሚሰማ የሙዚቃ አይነት ጋር ሊሄድ ይችላል፤በዚህም ፈጣን ሙዚቃ በሚሰማበት ወቅት የልብ ምት መጠን ይጨምራል፡፡
  • ትልቁ የሰውነት አካል ቆዳ ሲሆን ከኢንፌክሽን፣ ከአልትራቫዮሌት ጨረር እና ከድርቀት እንደ መከላከያ ሆኖ ያገለግላል። በተጨማሪም የሰውነት ሙቀትን ይቆጣጠራል፡፡
  • በእንቅልፍ ወቅት ማስነጥ አይቻልም፤ይህም አዕምሮ ማስነጠስን የሚቀሰቅሰውን ሪፍሌክስ ስለሚዘጋው ነው፡፡
  • የዓይን ጡንቻ ፈጣኑ የጡንቻ ዓይነት ሲሆን፤ዓይን ለሚኖረው እንቅስቃሴ ትኩረት አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
  • በውስጣዊ የጆሮ ክፍል የሚገኘው የ'ቬስትቡላር ሲስተም' ከዓይን እና 'ፕሮፕሪዮሴፕተር' ጋር በመጣመር ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
  • የሰው ልጅ በቀን 1.5 ሊትር የሚሆን ምራቅ የሚያመርት ሲሆን፤ይህም ለጥርስ መጠበቅ እና ለምግብ መፈጨት አስፈላጊ ነው፡፡በተጨማሪም በሙሉ የሕይወት ዘመን የሚያመርተው የምራቅ መጠን 25 ሺህ ኳርትስ ይሆናል ይህም 2 የመዋኛ ገንዳ መሙላት የሚችል ነው፡፡
  • አንድ ሰው በቀን በአማካኝ ከ28 ሺህ ጊዜ በላይ ዓይኑን ያርገበግባል ፤ ይህም በዓይን ውስጥ የሚገኘውን የእንባ እርጥበት በንጽህና በመጠበቅ እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡
  • የሰው አንጎል 75 በመቶው ውኃን ያቀፈ ሲሆን፤86 ቢሊዮን የነርቭ ሴሎችን ይዟል።በተጨማሪም ወደ 20 ዋት የሚጠጋ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል፤ይህም መጠነኛ አምፖልን ለማብራት በቂ ነው፡፡
  • በሰውነት ውስጥ በጣም ጠንካራ እና ረጅሙ አጥንት የጭን አጥንት ሲሆን፤ ከፍተኛ ጫና ከመቋቋም ባሻገር የላይኛውን የሰውነት አካል ክብደት ይደግፋል፡፡
  • ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰው ልጅ አካል ውኃ ነው፡፡
  • በአፎሚያ ክበበው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top