ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የዕለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

5 Mons Ago 349
ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የዕለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የዕለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅን ከአምራቾችና አቅራቢዎች በብቸኝነት እንደሚገዛ እና የሚገዛበትንም ዋጋ በየግዜዉ በመለዋወጥ አቅራቢዎችን እንደሚያበረታታ አስታውቋል፡፡

ስለሆነም፣ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዉጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ላይ ለዉጥ በማድረግ በገበያ የሚመራ የፖሊሲ ማእቀፍን ስለሚከተል ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል ብሏል ባንኩ ባወጣው መግለጫ፡፡

ወርቅ አምራቾችና አቅራቢዎች ይህንኑ በማወቅ የእለቱን የዉጭ ምንዛሪ ተመን ከብሔራዊ ባንክ ድረ-ገጽ ላይ በማገኘት ለሚያቀርቡት ወርቅ ክፍያዉን ወርቁን ከሸጡበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በእለቱ ማግኘት እንደሚችሉም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top