የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

13 ቀን በፊት
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፅኑ ፍቅር በመስቀል ላይ ያሳየበት እንዲሁም ይቅርታና ምህረትን ለሰው ልጆች የሰጠበት የጥልና የመለያየት ግድግዳን አፍርሶ የሰውን ልጅ የታደገበት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩት መንፈሳዊ በዓላት አንዱ ነው ሲሉም ተናግረዋል በመልዕክታቸው።

ይህ የትንሳዔ በዓል መታዘዝን፣ይቅርታንና ምህረትን እንዲሁም አንዱ ለሌላው መተሳሰብ እንዳለበት የሚያስተምረን ሲሆን መረዳዳትንና መጠያየቅን ከተለመደው ባህል ባለፈ በፍጹም መንፈሳዊነት ስሜት በጎዳና ላይ የወደቁትን በማሰብ፣በህግ ጥላ ስር ያሉትን በመጠየቅ፣ታመዉ የተኙትን በማጽናናትና ካለን ላይ በማካፈል በአብሮነት ትንሳኤውን የምናከብርበት በዓል ሊሆን ይገባልም ስሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በደል ተላልፎ በመሰጠት የሰውን ልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን ነጻ ለማውጣት ዋጋ የከፈለበት በመሆኑ እኛም አቅሜ ደካሞችን በመርዳትና ካለን በማካፈል ና ለወገኖቻችን በመድረስ ና በመተሳሰብ በዓሉን እንዲናከብር ጥሪ አቅርበዋል ።

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የትንሳኤ በዓል ለክልላችና ለሀገራችንና ህዝቦች እንዲሁን ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሰላም፣የበረከት፣ የመተሳሰብና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top