በየዓመቱ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞን በመምረጥ እውቅና የሚሰጠው የላውረንስ ስፖርት ለበጎ ተቋም ትላንት በስፔን ማድሪድ በ8 ዘርፎች የዘንድሮውን አሸናፊ ስፖርተኞችን በመምረጥ እውቅና ሰጥቷል፡፡
ላሊጋውን በአስር ነጥብ ልዩነት እያመራ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒንስ ሊግ ለግማሽ ፍፃሜ እንዲደርስ ገንቢ ሚና የተጫወተው ጁድ ቤሊንገሃም በዓመቱ ባሳየው ምርጥ ብቃት “Laureus World Breakthrough of the Year Award” ሽልማትን አሸንፏል፡፡
በሴቶች የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን የሆኑት የስፔን ብሄራዊ ቡድን የላውረንስ የ2024 ምርጥ ቡድን በሚል ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሴቶች ስፔናዊቷ አይታና ቦንማቲ በብሄራዊ ቡድን አንዲሁም በክለብ ባሳየችው ብቃት የላውረንስ የ2024 ምርጥ ሴት ስፖርተኛ በሚል ተመርጣለች፡፡
እንግሊዛዊቷ ሲሞና ቢሌስ ከጉዳት መልስ በጂምናቲክ ዘርፍ ባስመዘገበችው ውጤት የላውረንስ የ2024 ምርጥ ሴት ስፖርተኛ በሚል የተመረጠች ሌላኛዋ አትሌት ነች፡፡
በቴኒስ ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች የላውረንስ የ2024 ምርጥ ስፖርተኛ በሚል ለ5ኛ ጊዜ ሲመረጥ፤ ሆላንዳዊቷ አትሌት ዲዴ ድ ግሩፍ በአካል ጉዳት የሜዳ ቴኔሲ የላውረንስ የ2024 ምርጥ ስፖርተኛ በሚል ተመርጣለች፡፡
ስፖርትን ለበጎ ዓለማ በማዋል የላውረንስ የ2024 ምርጥ ስፖርተኛ በሚል የተመረጠው ስፔናዊው ራፋኤል ናዳል ነው፡፡
ትላንት ምሽት ለ25ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የላውረንስ ምርጥ ስፖርተኛ እና ምርጥ ቡድን አሸናፊዎች ሽልማት መርሃ ግብር ላይ ስመጥር ስፖርተኞች እና ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
በላሉ ኢታላ