አቶ አደም ፋራህ በአቶ ተዘራ ወልደ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ላይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አኖሩ

9 Mons Ago 1091
አቶ አደም ፋራህ በአቶ ተዘራ ወልደ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ላይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አኖሩ

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በአቶ ተዘራ ወልደ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ላይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በአቶ ተዘራ ወ/ማሪያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ አከባቢያቸው ተገኝተው ገልጸዋል።

አቶ አደም ፋራህ በሃዘን መግለጫቸው የአቶ ተዘራ ሞት እጅግ መሪር መሆኑን ገልፀው፤ አቶ ተዘራ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በትጋት ለመወጣት የሚያስችል ስብዕና እንደነበራቸውም ተናግረዋል።

እንደሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ አቶ ተዘራ ሀላፊነታቸውን በሚገባ የተወጡ አመራር እንደነበሩም ነው የገለጹት።

መላው የፓርቲ አመራርና አባላት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ አቶ ተዘራ ወ/ማርያም የጀመሯቸውን መልካም ተግባር ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ ተዘራ ወ/ማሪያም ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የአቶ ተዘራ ወልደማሪያም ሥርዓተ ቀብር በትዉልድ አካባቢያቸዉ ኮንታ ዞን አመያ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን፤ በስነ ስርዓቱ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል አቶ አደም ፋራህ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሌሎችም የፈዴራል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው መገኘታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል።

 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top