አቶ ታገሰ ጫፎ በኡጋንዳ የቀድሞ አፈጉባኤ መታሰቢያ መርሃ-ግብር ላይ ተሳተፉ

9 Mons Ago 782
አቶ ታገሰ ጫፎ በኡጋንዳ የቀድሞ አፈጉባኤ መታሰቢያ መርሃ-ግብር ላይ ተሳተፉ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢንቴቤ በተከበረው የቀድሞ የዩጋንዳ አፈጉባኤ ጃኮብ ኦላንያ መታሰቢያ የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ ታደሙ።

አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ በዝግጅቱ ላይ የተገኙት በዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቬኒ ግብዣ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

በወጣቶች ላይ ባተኮረው በዚህ የመታሰቢያ መርሀ-ግብር ላይ አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት ንግግር፤ የአፍሪካ ወጣቶች በአፍሪካዊ እሴቶች እና ማንነት አንፆ መቅረፅ ይገባል ብለዋል።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top