ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደረገ

9 Mons Ago 784
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደረገ
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደረገ።
 
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት በሥነ-ምግባሩ እና በወታደራዊ አቅሙ በዓለም አቀፍ ተቋማት ተፈላጊ እና ተመራጭ እየሆነ መጥቷል፡፡
 
የፖሊስ መኮንኖቹ በስምሪታቸው የኢትዮጵያ ፖሊስ አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚያመላክት የላቀ ሥነ-ምግባርና ፖሊሳዊ ሙያ ሊያሳዩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
 
መሰል ዓለም አቀፍ ተሳትፎ የሚጠይቁ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው፤ ለሰላም አስከባሪ ተጓዦች ተልዕኳቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
 
የፌደራል ፖሊስ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ኮማንደር ተገኝ አጋዥ በበኩላቸው፤ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በአብዬ ግዛቶች እንዲሁም በሐይቲ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ አመራሮች የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት በመወጣት የሀገራቸውንና የተቋማቸውን መልካም ገጽታ መገምባታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የሴት ፖሊስ ተሳታፊዎች ቁጥር እስካሁን ከነበረው የሰላም መስከበር ስምሪት በቁጥር ብልጫ ያለው እና 11 ሴት አመራሮች የሚሳተፉበት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top