በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኀብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የቦሮ-ሽናሻ ልማት ማህበር ገለጸ

9 Mons Ago 1066
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኀብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የቦሮ-ሽናሻ ልማት ማህበር ገለጸ

የቦሮ-ሽናሻ ልማት ማህበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ የብሔረሰብ የልማት ማህበራት ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ20 ዓመት በፊት በቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ ተወላጆች የተመሠረተ የልማት ማህበር ነው፡፡

የማህበሩ አባላት እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ጨምሮ  የተለያዩ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ በአሶሳ ከተማ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አስማማው ዘገዬ፤ የልማት ማህበሩ በመተከል ዞንና በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስትን የሚያግዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ማህበሩ በትምህርት፣ በጤና በግብርና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አና በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሰማራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ አጋር አካላትን በማሳተፍ ሲሰራ መቆየቱን የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢ አቶ አሰፋ ናሮ ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ የሽናሻ ብሔረሰብን ባህላዊ ጭፈራዎች፣ አልባሳት እና አመጋገብን ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

የልማት ማህበሩ ዛሬ እያካሄደ ባለው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ፤ በማህበሩ የ2023 (እኤአ) የስራ አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖርት ላይ እንዲሁም የ2024 ዕቅድና የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡

በጀማል አሕመድ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top