ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በሁሉም መስኮች ተስፋ ሰጪ እና አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡- ርዕሰ መስተደሰድር ኦርዲን በድሪ

9 Mons Ago 813
ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በሁሉም መስኮች ተስፋ ሰጪ እና አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡-  ርዕሰ መስተደሰድር ኦርዲን በድሪ
"ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ በሐረሪ ክልል ሲካሄድ የቆየው ኮንፍረንስ ተጠናቋል።
 
በኮንፍረንሱ ባለፉት2 ዓመታት ተኩል የተከናወኑ ተግባራት ያስገኙት ውጤት እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
 
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ የተጀመሩ የሰላም እና የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራዎችን በማጠናከር የክልሉን አንፃራዊ ሰላም ወደ አዎንታዊ ሰላም ማሳደግ ይገባል፤ ለዚህም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
 
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የቀሪ ምርጫ ዘመን የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተደሰድሩ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ለመፍትሄው በጋራ መስራት የሚገባ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
 
ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን መታገል እና ማስወገድ ተገቢ መሆኑን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መንግስት በሚያከናውናቸው ተግባራት ሁሉም የመሪነት ሚናን በመወጣት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
 
የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈተረቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ፤ በቀጣይ በኮንፍረንሱ የተነሱ የስራ አጥነት ፣ የኑሮ ውድነት እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
 
በየዘርፉ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የህዝብን ቁልፍ ጥያቄ ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
 
በቀጣይ የማስፈፀም አቅምን በመገንባት ውጤታማ ስራዎችን ማጠናከር ተገቢ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።
 
በቴዎድሮስ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top