መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ600 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

1 Mon Ago
መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ600 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ600 በላይ ተማሪዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 201 ያህሉ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛዉ እና በተከታታይ መርሀ-ግብር ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ ከነበሩት 479 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ 152ቱን ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ ማስመረቁ ተጠቅሷል፡፡

ተመራቂዎቹ በጤና ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ   እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውም ተገልጿል። 

በሚፍታህ አብዱልቃድር


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top