"ፀሐይ" አውሮፕላን ለሀገሯ የምትበቃበት ስምምነት መፈረሙ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

2 Mons Ago
"ፀሐይ" አውሮፕላን ለሀገሯ የምትበቃበት ስምምነት መፈረሙ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ኢትዮጵያ ሰራሿ "ፀሐይ" አውሮፕላን ለሀገሯ የምትበቃበት ስምምነት መፈረሙ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ "በ1928 በኛው ውጥንና ባለሙያና በውጭ አዋቂ ተሳትፎ የተሰራችው ፀሐይ አውሮፕላን ለሀገሯ የምትበቃበት ስምምነት ተፈርሟል" ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤ "መልካሙ የታሪካችን ገፅታ ይመለሳል፣ አዲስ ታሪክ ይሰራል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡  


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top